![]() |
|
|
Home Programs About Us Contact |
|
የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ (ኢሕድ)
ማሳሰቢያ የነፃነት ለኢትዮጵያ ሳምንታዊ ራዲዮ መርሐ ግብር በዚህ ድረ ገፅ ላይ በየሳምንቱ ይደመጣል
ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Nov 02, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Oct 25, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Oct 19, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Oct 05, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Sep 28, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Sep 21, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Sep 14, 2008 ነፃነት ለኢትዮጵያ Sun. Sep 7, 2008
የዚህ ሳምንት ዝግጅት በቅድሚያ ዜና በማስከተልም ሳምንታዊው የነፃነት ለኢትዮጵያ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ይለጥቃል መልካም ቆይታ
I
(ጎንደር ኢ.ሕ.ድ.) አለመረጋጋት እና የፖለቲካ ነውጥ ውስጥ የወደቀው የመለስ አገዛዝ በጎንደር ከተማ መውጫና መግቢያ ፍተሻና ምርመራ ይዟል፤ ተቃውሞውም እንዳይዛመት ስጋት ላይ ወድቋል።
(ገለምሶ ኢ.ሕ.ድ.) ተማሪወችና የወያኔ ታጣቂወች ተፋጠዋል፤ አንዲት ሴት ወጣት ተማሪ በጥይት በግፍ ተገደለች ብዙወችም መጎዳታቸው ታወቀ
(ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) በጎጃም ክፍለ ሀገር በብርሸለቆ ማሰልጠኛ ጣቢያ በሺህ የሚቆጠሩ ከትግራይ እና ከወሎ የተመለመሉ ወታደሮች ለስልጠና መግባታቸውን የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ የዜና ወኪል አስታወቀ
ለዝርዝር ዜናዎች Tue. April 04, 2006 ይዳስሱ
(አ/አ ኢ.ሕ.ድ.) በአ/አበባ የፈንጅ ፍንዳታ አንድ ሰው ተገደለ ብዙወችን አቆሰለ ፤ አገዛዙ ሕዝቡን ለማሸበር ለማሸበር ነው ተባለ። (ሐረርጌ ኢ.ሕ.ድ.) በሐረርጌ አለማያ ዮኒቨርስቲ ተቀስቅሶ ነበር ፤ ተማሪወች በታጣቂወች ተደብድበዋል (ጋምቤላ ኢ.ሕ.ድ.) በጋምቤላ ክልል ከዲማ በቅርብ እርቀት በምትገኝ ልዪ ስፍራዋ ገሠና ተብላ በምትታወቀው ቀበሌ አማፂያን በወያኔ ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት አደረሱ (ዋሽንግተን ዲሲ ኢ.ሕ.ድ.) በአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳይ ንዑስ ኮሚቴ የኢትዮጵያን ጉዳይ በተመለከተ የቀረበውን HR4423 የሕግ ረቂቅ የተተራሰ ምስክርነት ዛሬ ይደመጣል ለዝርዝር ዜናዎች Tue. Mar 28, 2006 ይዳስሱ
(አ/አ ኢ.ሕ.ድ.) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ፤ ሰብዓዊ መብቶችን ይዞታ 24ኛ መደበኛ መግለጫውን ይፋ አደረገ። (አ/አ ኢ.ሕ.ድ.) ያለፈው እሮብ የወያኔ አስቂኙና የይስሙላው ፍርድ ቤት ውሎ (ሸዋ ኢ.ሕ.ድ.) በሸዋ ክፍለ ሀገር በጎሀጺዪን የተማሪወች የተቃውሞ ዓመፅ ተነሣ ፡ በመቶ የሚቆጠሩ ተማሪወች መታሰራቸውን የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ የዜና ወኪል አስታወቀ (ሸዋ ኢ.ሕ.ድ.) በአምቦ እና በአዲስ አበባ መካከል በምትገኘው የጊንጪ ከተማ የተማሪወች ዓመፅ አይሏል ፡በርካታ የመንግስት መኪናወች መሰባበራቸውን የደረሰን ዜና አስታወቀ (ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) በመላው የጎጃም ክፍለ ሐገር የቅንጅት ለአንድነት እና ለዲሞክራሲ ደጋፊ እና አባላት ላይ ያነጣጠረ የሽብር ዘመቻ ወያኔ እያካሄደ መሖኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ፤ በዚህም ሽብር ሰለባ ከሆኑት መካከል፤ በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በገደብ ቀበሌ ሁለት ወጣቶች ተገደሉ ፤ በእነማይ ወረዳ በራባት አንዲት ሴት ልጅ ተደብድባ በግፍ ተገደለች እንዲሁም በጣቢት ሚካዔል አንድ አረጋዊ በአሰቃቂ ዘግናኝ ሁኔታ ተገደሉ። (አ/አ ኢ.ሕ.ድ.) ወያኔ ካድሬወቹን በመላው የሀገሪቱ የገጠር ክፍል ለማሰማራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከውስጥ አወቅ ምንጮቻችን ለማወቅ ተቻለ ፤ የእነኝህ ካድሬወች ተልእኮ አርሶ አደሩን የኢህአደግ ደጋፊ ለማድረግ የመጨረሻ ጥረት ለማድረግ እንደሆነ ፤ በሌላ በኩል በከተማ ውስጥ በማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት በስልጣን ላይ ወደፊትም መሆን የሚችል የኢህአደግን የፓርቲ ደብተር የያዘ መሆን እንዳለበት ተግባራዊ እንደሚሆን የውስጥ አወቅ ምንጮቻች አክለው ገልጠዋል። (ጎንደር ኢ.ሕ.ድ.) በሰሜን ጎንደር ታች አርማጭሆ ወረዳ የወያኔ ነፍጠኞች አማፂያንን ትረዳላችሁ በሚል ነዋሪውን ቁም ስቅሉን እያሳዩት መሆኑን በተለየም ደግሞ የአብረሀ ጅራ ነዋሪወች ላይ የቤት ለቤት አሰሳ በማለት ለፍልሰት መዳረጋቸውን የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ ምንጮች አረጋግጠዋል (ደቡብ ኢትዮ ኢ.ሕ.ድ.) በደቡብ ኢትዮዽያ የምግብ እጥረቱ እንዳጠላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ለዝርዝር ዜናዎች Sat. Mar 25, 2006 ይዳስሱ
(ዲማ ኢ.ሕ.ድ.) ከጅማ ከተማ በ90 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምትገኘው ዲማ ከተማ ወጣ ብሎ በድምሩ አምስት የሲዳማ ዞን ካቢኔ አባላት እና የወያኔ ሬዲዮ ፋና ጋዜጠኞች ተገደሉ፤ ሶስቱ ደግሞ ከፍተኛ መቁሰል የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ ቃል አቀባይ ገለጠ።
(ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) በጎጃም ክፍለ ሀገር በዳንግላ ወረዳ የ32ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር ባልደረቦች የሆኑ ስድስት የሠራዊቱ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ተሰወሩ።
(ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) እነማይ ወረዳ የበላይ ዘለቀ መሰናዶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አና የብቸና መካካለኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወይም በቅጽል ስሙ ዳርፉር በመባል የሚታወቀው ተማሪወች አገዛዙን በመቃወም ከተማዋን አምቀዋት ዋሉ፤ እዚያው በጎጃም ክፍለ ሀገር በእናርጅ እናውጋ ወረዳ ደግሞ አራት መምሕራን በወያኔ አገዛዝ ወህኒ በት ታሰሩ።
(ገብረ ጉራቻ ኢ.ሕ.ድ.) በገብረ ጉራቻ የኩዪ ሁለተኛ ደለጃ ት/ቤት ተማሪወች ተቃውሞ አሰሙ፤ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ወደ መጡበት ተመለሱ።
(ጎንደር ኢ.ሕ.ድ.) በአብደራፊ የወያኔ የግብርና እና የገጠር መሠረተ ልማት ሠራተኞች ታፍነው ተወሰዱ።
(ጅማ ኢ.ሕ.ድ.) በደቡብ ኢትዮዽያ ሚዛነ ተፈሪ በየተለጣፊው መምሕራን ማሕበር ሊቀመንበር አቶ አማኑዔል ፓውሎስ የተጠራው ስብሰባ ተቃውሞ ገጠመው።
(አ/አ ኢ.ሕ.ድ.) የወያኔው ሕገወጥ የአ/አበባ ከኒቲባ አርከበ እቁባይ በግፍ የታሰሩትን የቅንጅት እና የሙያ ማሕበራት አመራር አባላት የፍርድ ችሎት ወደ ቃሊቲ ቀበሌ 08 ለማዛወር በዝግጅት ላይ መሆኑን ከውስጥ አወቅ ምንጮች ለማወቅ ተቻለ።
(ምሥራቅ ኢትዮዽያ ኢ.ሕ.ድ.) የኢትዮዽያ ንብረት በበርበራ ወደብ ረጅም ጊዚያት መቀመጥ ችግር እየፈጠረ መሆኑን የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ የዜና ወኪል አስታወቀ
(ካርቱም ኢ.ሕ.ድ.) ሱዳን የወያኔ ጦር ድንበሬን ጥሶ ገባ በማለት ከሰሰች
(ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) በሕገወጡ የአድዋ ተወላጅ አባ ፓውሎስ የሚመራው ኢትዮዽያ ቤተክህነት በገጠር አጥቢያ የሰበካ ጉባዔወች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፤ሕዝበ ክርስቲያኑ ተቆጥቷል።
ለዝርዝር ዜናዎች Tue. Mar 21, 2006 ይዳስሱ
ለዝርዝር ዜናወች እና ለቀሪ ዝግጅቶች ይችን ሊንክ Sat. Mar 18,2006 ይዳስሱ
(ኢ.ሕ.ድ.) የአቶ መለስ ቡድን የሄጉን የፍርድ ውሳኔ ለመቀበል ተስማማ፤ ከወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጋይነት ወደ ሠራዊቱ የተቀላቀሉት እንዳያምፁ ተሰግቷል(ኢ.ሕ.ድ.) በፀረ ወያኔ ሰላማዊ ትግል ጊንጪ ከተማ ስትናጥ ሰነበተች፤ የፌደራል ሠራዊት በሰላማዊው ሕዝብ ላይ የጥይት ሩምታውን ማዝነቡን በስፍራው የተገኘው የኢ.ሕ.ድ ዘጋቢ ገለጠ(ኢ.ሕ.ድ.) የሐረር ከተማ የወያኔ ምክር ቤት በፈንጅ ተመታ(ኢ.ሕ.ድ.) የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ኢትዮዽያን የተመለከተውን ዘገባ ዛሬ ይፋ ያደርጋል፤ የቡድኑ መሪ ወ/ሮ አና ጎሜዝ አ/አበባ እንዳይገቡ ተከለከሉ(ኢ.ሕ.ድ.) ወጣት ጋዜጠኛዋ ፍሬዘር ነጋሽ ከእስር በዋስ ተለቀቀች፤ ሌላ ጋዜጠኛ የ አንድ ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት
ለዝርዝር ዜናወች እና ለቀሪ ዝግጅቶች
ይችን ሊንክ
የቅዳሜ መጋቢት 02 1998 የኢትዮዽያ ሕዝብ ዜና ዝርዝር
ቀይ ሽብር በጎንደር
በጎንደር ከተማ ልዪ ቦታዋ አየር ማረፊያ በመባል የሚታወቀው አካባቢ አራት ወጣት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪወች ማለትም
ሰኞ ጥር 29፣ 1998 ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በአደባባይ ጭካኔ በተሞላበት በወያኔ በቀይ ሽብር መገደላቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት መዘገባችን ይታወሳል እናም የዛሬው መርሀ ግብራችን ያነጣጠረው በዚሁ በግፍ ከተረሸኑት ቤተሰቦችጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ነው
ኢትዮዽያዊያን እህቶቻችን የአለም አቀፍ የሴቶችን ቀን በWhite House ደጃፍ አከበሩ
የ March 8th የአለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮዽያዊያን እህቶቻችን የሰላም የልማትና የ እርዳታ ድርጅት በሚል ስያሜ ላለፉት 16 ዓመታት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሴቶች እህቶቻችን በ አሜሪካ የመንግሥቱ መኖሪያ በሆነው White House ተሰባስበው በሐገራችን ኢትዮዽያ በግፍ በጭቆና ቀንበር ላይ ለሚገኙት ሴቶች አጋርነታቸውን በማሳየት ሻማ በማብራት ጸሎት አድርገዋል እናምይህንን በተመለከተ ከአዘጋጅ ኮሚቴ መሪ ከነበሩት ከዶክተር ማይገነት ሽፈራው ጋርም ውይይት አለን
የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ ርዕሰ አንቀፅ ወይንም ቀዳሚ ቃል ደግሞ ያነጣጠረው በነፃው ጋዜጣ ላይ ነው እናም
ለዝርዝሩ የቅዳሜ የካቲት 19 1998 ፕሮግራም ይችን ሊንክ
የማክሰኞ የካቲት 28 1998 የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ ርዕሰ ዜናወች ጎጃም ኢ.ሕ.ድ.) በባሕር ዳር ከተማ ሁለት የወያኔ መንግሥት ሹማምንት ተገደሉ አራት የወያኔ ታጣቂወች ደግሞ እዚያው ጎጃም በአክሻ ወረዳ ግምጃቤት ከተማ ልዪ ቦታዋ አዘና ተብላ በምትጠራ መንደር ታፍነው መገደላቸውን የኢትዮዽያ ሕዝብ ድምፅ (ኢ.ሕ.ድ) ቃል አቀባይ ገለጠ (ደጀን ኢ.ሕ.ድ.) ነዋሪነታቸው በሙሽሪት ድንጋይ የሆኑ እና ከፍተኛ አክብሮትና ተፈሪነት ያላቸው አቶ አንዳርጋቸው ካሤ ከ20 ያላነሱ አባ ወራወችን በማስተባበር ወደ ጫካ መግባታቸው ሲሰራጭ አካባቢውን ለማሳመፅ የሚችሉ ናቸው በማለትም አገዛዙ አባብሎ ለማስመለስ ሙከራ ላይ መሆኑን በስፍራው ለተገኘው የኢ.ሕ.ድ ዘጋቢ አካባቢወች ገለጡ
(ጎንደር ኢ.ሕ.ድ.) በመተማ እና አብደራፊ መካከል ልዪ ስፍራዋ ግራር ውሃ በተባለች ሥፍራ በወያኔ ላይ ጥቃቱ አይሏል የመለስ መንግሥት መደናገጥ ከፍቷል
(ከፋ ኢ.ሕ.ድ.) በደቡብ ኢትዮዽያ ሚዛነ ተፈሪ ኗሪወች ላይ በደል እያደረሰ ነው የውሃ እና የመብራት አገልግሎት ለወራት ተቋርጧልም ለዝርዝር ዜናዎች
Tue. Mar 07, 2006
ይዳስሱ
የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምፅ (ኢሕድ) ሬዲዬ ዘወትር ማክሰኞ እና ቅዳ ሜ ከምሸቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት በ 7590 kHz ወይም 41 ሚትር ባንድ አጭር ሞገድ ወደ ኢትዮጵያ ይሰራጫል
Last Week Archives
Archives February 2005 Saturday
Feb 25, 2006
Tuesday Feb 21, 2006
Saturday
Feb 18, 06
January 2005 Saturday Jan 28-06 Tuesday
Jan-24-06
Saturday
Jan-21-06
Tuesday Jan 03-06
December 2005
Saturday Dec 31-05
Tuesday Dec 27-05
Saturday
Dec 24-05
Saturday Dec 17-05
|
|
© 2005 voep.net |